TPLF is getting Ready to implement the Master killer:--‹‹የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን በአዲሱ ዓመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል››

01 September 2015 ተጻፈ በ       

አቶ ኃየሎም ጣውዬ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 54 ሺሕ ሔክታር መሬት ስፋት አለው፡፡ አስተዳደሩ በአሥር ክፍላተ ከተሞችና 116 ወረዳዎች የተዋቀረ ነው፡፡ በዚህ የአስተዳደር ክልል ውስጥ የሚገኙ ይዞታዎች በመንግሥት፣ በግለሰብና በማኅበረሰብ

የተያዙና  በበቂ ያልተደራጀ በመሆናቸው፣ ለሙስናና ለሕገወጥ ድርጊቶች ተጋላጭ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች አዲስ አበባን የመሩ የአስተዳደሩ አካላት እነዚህን ችግሮች ለማስተካከል ሙከራዎችን ቢያደርጉም፣ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የተደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 እስከወጣ ድረስ ለውጥ አልታየባቸውም፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም በብዙ አደረጃጀቶች ያለፈው የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር በቢሮ ደረጃ በድጋሚ ተዋቅሮ ‹‹የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ›› ሆኖ ተደራጅቷል፡፡ ቢሮው በሥሩ ሰባት ኤጀንሲዎች ያሉት ሲሆን፣ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች አሉት፡፡ ሰባቱ ዘርፎች የተቀናጀ መሬት ማዕከል ከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ፣ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤትና የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ ናቸው፡፡

አቶ ኃየሎም ጣውዬ አራቱን የመሬት ዘርፍ ኤጀንሲዎች ይመራሉ፡፡ ቢሮው ከሊዝ አዋጅ በመነሳት ከመሬት ጋር የተገናኙ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች አውጥቷል፡፡ የሰው ኃይሉን መንግሥት የሚፈልገውን ሥራ ማካሄድ በሚያስችል መልኩ እንደቀረፀም እየተነገረ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በዘርፉ በርካታ ቅሬታዎች ይነሳሉ፡፡ አገልግሎት አሰጣጡም ዝግመት ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ተገልጋዮችን በማጉላላት የታጀበ እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ሙስና አሁንም ቢሆን በዘርፉ የሚስተዋል ችግር ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ተግባራዊ ሳይሆን መዘግየት ከሚነሱት መካከል ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃየሎም ጣውዬን ውድነህ ዘነበ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በ1995 ዓ.ም. የተዘጋጀው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በ2005 ዓ.ም. የመጠቀሚያ ጊዜው አብቅቷል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላ የወጣ ማስተር ፕላን ባለመኖሩ በምን እየተመራችሁ ነው ያላችሁት?

አቶ ኃየሎም፡- መዋቅራዊ ፕላኑ የመጠቀሚያው ጊዜ እንደተጠናቀቀ እኛ ክፍተት አልፈጠርንም፡፡ አንድ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በማቋቋም በተለይ ዳግም አዲስ አበባንና በዙሪያዋ ያሉት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎችን በማካተት መዋቅራዊ ፕላን ለማዘጋጀት ተሞክሯል፡፡ የፕላን ዝግጅቱ በጥሩ መንገድ እየሄደ ነው፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑ በካቢኔ ስላልፀደቀ ተብሎ ያጋጠመ ችግር የለም፡፡ ለምን ቢባል ወዲያውኑ ቢፀድቅ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ማስተር ፕላን የሚያዘጋጀው ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የኦሮሚያ አካባቢዎችን አቀናጅቶ ነው እየሠራ ያለው፡፡ አዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችም የየራሳቸው መዋቅራዊ ፕላን አላቸው፡፡ እንደየባህሪያቸውና እንደየአስተዳደራዊ ድንበራቸው የየራሳቸው ፕላን አላቸው፡፡ ስለዚህ እኛ የአዲስ አበባ ክልል መዋቅራዊ ፕላን አለን፡፡ ሁለቱን አቀናጅቶና አዋህዶ የሚሰሠራ ‹‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጽሐፈት ቤት›› ተቋቁሟል፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑም ተሠርቷል፡፡ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ የሠራውን መዋቅራዊ ፕላን ረቂቁን ለአዲስ አበባ  ለአስተዳደር አስረክቧል፡፡ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ደግሞ የተዘጋጀውን ረቂቅ ማስተር ፕላን ለካቢኔ አቅርቦ ያስወስናል፡፡ 

ሪፖርተር፡- ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ለአዲስ አበባም ሆነ ለአሮሚያ ልዩ ዞን ይበጃል ያለውን መዋቅራዊ ፕላን አዘጋጅቷል፡፡ ነገር ግን መዋቅራዊ ፕላኑን አፅድቆ ሥራ ላይ በማዋል በኩል መዘግየት የለም ይላሉ?

አቶ ኃየሎም፡- በዋነኝነት የዘገየ ነገር የለም፡፡ እኔ ውስጡ ስላለሁ አውቀዋለሁ፡፡ ቀደም ሲል መዋቅራዊ ፕላን አዘገጃጀትን አፅድቀን እንበትናለን፡፡ የድሮ ማስተር ፕላን ግትርነት ያጠቃዋል፡፡ የአሁኑ ደግሞ የሚያሠራ ነው፡፡ የምታስተካክለው ነገር ይኖራል፡፡ የድሮው ከፀደቀ በኋላ ለማስተካከል ያስቸግራል፡፡ ያሁኑን መዋቅራዊ ፕላን ግን ማስተካከል ትችላለህ፡፡ በአዲሱ መዋቅራዊ ፕላን በርካታ ነገሮችን በሒደት ማስተካከል ችለናል፡፡ አሁን እንዲያውም እንዳጋጣሚ ሆኖ መዘግየቱ በራሱ ለአዲሱ መዋቅራዊ ፕላን ትልቅ ግብዓት ሆኗል፡፡ በተካሄዱ በርካታ የውይይት መድረኮችና በሥራ ሒደቶች ብዙ መስተካከል ያለባቸውን ክፍተቶች ነቅሰን በማውጣት እንዲስተካከሉ አድርገናል፡፡ 

ሪፖርተር፡- መዋቅራዊ ፕላኑ በ2008 ዓ.ም. ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል ማለት ይቻላል?

አቶ ኃየሎም፡- እንደኔ ግምገማ በትክልል በ2008 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ አዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን አካባቢዎችና ከተሞች የየራሳቸው መዋቅራዊ ፕላን ይኖራቸዋል፡፡ ይህ ማለት በአጭር ቋንቋ የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት እነዚህን መዋቅራዊ ፕላኖች ማለትም የሁለቱን የአስተዳደር አካላት መዋቅራዊ ፕላን ያቀናጃል ማለት ነው፡፡ ይህ ግሩም ሐሳብ ነው፡፡ ልዩ ዞኑና እኛም ሠርተናል፡፡ የማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት ያቀናጀውን መዋቅራዊ ፕላን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ክልል ውስጥ የሚገኘውን መዋቅራዊ ፕላን በ2008 ዓ.ም. ያፀድቃል፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ዞንም ያፀድቃል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በእርግጥ እየዘገየ ከሄደም የራሱ ችግር አለው፡፡ ባልፀደቀ መዋቅራዊ ፕላን መጠቀም ሕገወጥነት ነው፡፡ ስለዚህ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ መዋቅራዊ ፕላኑ ሕጋዊ እንዲሆንና ችግሮች እንዳይፈጠሩ በአዲሱ መዋቅራዊ ፕላን ለመጠቀም የሚያስችል ሥራ ሠርቶ ያፀድቃል፡፡ በመዋቅራዊ ፕላኑ ላይ ሁሉም አመራር ሙሉ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት ያዘጋጀውን መዋቅራዊ ፕላን ለውይይት ባቀረበበት ወቅት ከፍተኛ  አለመግባባት ፈጥሮ ነበር፡፡ ባለመግባባቱ የተነሱ ሐሳቦችን መንግሥት ከግንዛቤ አስገብቷል ማለት ይቻላል?

አቶ ኃየሎም፡- እነዚህ አካባቢዎች በተቀናጀ መንገድ ቢያድጉ ሁሉም ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ማንም ይኼን ያምንበታል፡፡ ይህንን ድንቅ ሐሳብ አዕምሮውን ክፍት አድርጎ የመተለከተ ሁሉ የሚያደንቀው ነው፡፡ ነገር ግን በሌላ ትርጉም የሚመለከት ሰው አይደኖርም ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ አመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ይሠራል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑ ከተጠናቀቀ በኋላ እንዴት ነው የሚፀድቀው? እንዴት ነው ተግባራዊ የሚሆነው? እንዴት ነው የምንመራው? የሚለው ጉዳይ የሚታይ ይሆናል፡፡ መዋቅራዊ ፕላን ላይ ግንዛቤ መፍጠር በአንድ ወቅት ተሠርቶ የሚያልቅ አይደለም፡፡   

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጽሕፈት ቤት ቦርድ በዚህ ላይ አቅጣጫ ሰጥቷል?

አቶ ኃየሎም፡- እስካሁን የሰጠው አቅጣጫ የለም፡፡ በሌሎች ሥራዎች ተጠምደን ነው ያለነው፡፡ አንተም ታውቃለህ፡፡ የምርጫ ሥራ፣ የሥራ አፈጻጸም ግምገማና ለቀጣይ ዓመት የዝግጅት ሥራዎች ውስጥ ስለነበርን ወደዚህ ሥራ አልገባንም፡፡ ዞሮ ዞሮ አሁን ያለውን ያያል፡፡ በዋነኛነት እኛ ግን የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን ግብዓት ጨምረን እናፀድቃለን፡፡ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ጋርም እየሠራ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተለያዩ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡ ለምሳሌ ውኃ ሲያገኝ፣ ፍሳሽ ቆሻሻ ደግሞ ይደፋል፡፡ የግድ የጋራ ጥቅም መከበር ስላለበት፣ የጋራ መግባባት ላይ መደረስ አይኖርበትም?

አቶ ኃየሎም፡- እኔ በሙያዬ ፕላነር ነኝ፡፡ የሪጅናል መዋቅራዊ ፕላን በእኛ አልተጀመረም፡፡ በሌሎች አገሮች በሰፊው ይሠራበታል፡፡ ግለሰቦች ከግንዛቤ ጉድለት ወይም ሆን ብለው ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ማቀናጀት ምን ማለት ነው? የተወሳሰበ ጉዳይ አይደለም፡፡ አንተ እንዳልከው ቁምነገሩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ጉዳዮችን እንዴት እናሳድግ የሚለው ነው፡፡ የአንድ አካባቢ ዕድገት ከተጎራባቹ ጋር አብሮ መሄድ ይኖርበታል፡፡ የአዲስ አበባ ዕድገት በዙሪያው ያለውን ይዞ መሄድ አለበት፡፡ አዲስ አበባ ውኃ ከልዩ ዞኑ ትጠቀማለች፡፡ ሌሎች ሰፋፊ ጥቅሞች ይኖራሉ፡፡ በተመሳሳይ ልዩ ዞኑም ከአዲስ አበባ የሚጠቀመው ይኖራል፡፡ መንገድ ስትሠራና ባቡር ስትዘረጋ አንድ ላይ የተሳሰረ ነው፡፡ መዋቅራዊ ፕላኑ ለሁሉም የሚበጅ ግዙፍ ዕቅድ ነው፡፡ የሁለትዮሽ ጥቅምን በሚመለከት መንግሥት የጠራ ግንዛቤ አለው፡፡ የጋራ ማስተር ፕላኑ ይህንን ከግንዛቤ ከቶ የተዘጋጀ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- መንግሥት በዕድገትና ትራንስፎርሜሸን ዕቅዱ ለማፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በርካታ የማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክቶች ለካቢኔ ቢቀርቡም ውሳኔ ግን እያገኙ አይደለም፡፡ ካቢኔው ውሳኔ የማይሰጥበት ምክንያት ምንድነው?

አቶ ኃየሎም፡- መሬት የሚቀርበው በጨረታና በምድባ ነው፡፡ መሬት በጨረታ በማቅረብ በኩል በግምገማችን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡ በየወሩ ጨረታ እናወጣለን፡፡ ነገር ግን በብዛት ማውጣት እንዳለብን  እናውቃለን፡፡ ይኼ ጉዳይ በቀጥታ እኔን የሚመለከት ባይሆንም፣ ባካሄድ ነው ግምገማ መሬት በሰፊውና በብዛት ማውጣት እንዳለብን ገምግመናል፡፡ ከ2006 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት ጀምሮ ያለምንም መዛነፍ በየወሩ መሬት ለጨረታ ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ በምደባ አግባብ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ይሰጣል፡፡ በነገራችን ላይ ካቢኔው ራሱ ከሌሎች ጉዳዮች ይልቅ በመሬት ጉዳይ ላይ ተጠምዷል በሚል የመሬት ጉዳይ ካቢኔ ሆኗል እየተባለ ነው፡፡ የመሬት ጉዳይ በብዛት እየታየ ነው፡፡ ነገር ግን እንደዚያም ቢሆን በሚፈልገው ልክ እልታየም በሚለው ጉዳይ እኔም እስማማለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የከተማው አስተዳደር በሊዝ መመርያና ደንቡ አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች ትኩረት እንደሚሰጥ አስቀምጧል፡፡ ነገር ግን የሆቴል፣ የሪል ስቴት፣ የትምህርትና የጤና ተቋማት ለመገንባት በርካታ ባለሀብቶች የመሬት ጥያቄ እየቀረቡ ቢሆንም ጥያቄዎች እየተስተናገዱ ግን አይደለም፡፡ ምናልባት የሊዝ ደንብና መመርያ እንዲሻሻል መወሰኑ እነዚህን የአገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች ለማስተናገድ ይሆን?

አቶ ኃየሎም፡- በነገራችን ላይ የሊዝ አዋጅ የፈታችው በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ኪራይ ሰብሳቢነትን የሊዝ አዋጁ ተዋግቷል፡፡ ምንም እሴት ሳይኖር ሀብት የሚፈጥሩ ነበሩ፡፡ አመራሩም ፈጻሚውም ግለሰቦችን የማገልገል አዝማሚያ ያሳዩ ነበር፡፡ ፍትሐዊነት የለም ነበር፡፡ ይኼ ክፍተት የተሞላው በሊዝ አዋጁ ነው፡፡ መሬት የሚቀርበው በጨረታና በምደባ ያደረገው የሊዝ አዋጅ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ አላሠሩ ያሉ ጉዳዮች በመኖራቸው የሊዝ ደንብና መመርያውን ለማስተካከል እየተሠራ ነው፡፡ በ2008 ዓ.ም. ከምናያቸው የሕግ ማዕቀፎች አንዱ የሊዝ መመርያና ደንብ  ነው፡፡ 

ሪፖርተር፡-  ሕገወጥ ባለይዞታዎች ሕጋዊ ለማድረግ እየሠራችሁ ነው፡፡ ሥራው ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

አቶ ኃየሎም፡- አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ 60 ሺሕ ይዞታዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሕገወጦች ለማስተናገድ ተሞክሯል፡፡ ከዚህ በኋላም ከ1988 እስከ 1997 ዓ.ም. ደግሞ ሕገወጥ ባለይዞታዎችን ሕጋዊ መሆን አለባቸው፣ ለመንግሥትም ይጠቅማል፡፡ ለግለሰቦችም ይጠቅማል፡፡ ለወደፊቱም በፕላን ለመመራት ከዚያም በዘለለ የማይንቀሳቀሰ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ወደ ሥራ በሚገባት ጊዜ እንቅፋት አንዳይሆኑ መፍትሔ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ወደ ሥራ በሚገባበት ጊዜ እያንዳንዱ መሬት ተመዝግቦ መብት ሊፈጠር ይገባል፡፡ በዚህ መሠረት በተካሄደው ጥናት 44,547 ይዞታዎች ሕገወጥ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ ሊበልጥም ሊያንስም ይችላል ተብሎ ነው ወደ ሥራ የተገባው፡፡ የሚያስፈልጉ የሕግ ማዕቀፎች አውጥተናል፡፡ መመርያ 17/2006 አሻሽሎ በማውጣት የቀድሞው ጭምር ከ1988 ዓ.ም. በፊት ያልተስተናገዱትንም እናስተናግዳለን ብለናል፡፡ ይህን ሁሉ የምናደርገው ዘመናዊ ወደሆነ የመሬት አስተዳዳር ለመግባት ካለን ራዕይ ከመነሳት አኳያ ነው፡፡ የከተማችን ዋና ዋና ትላልልቅ ችግሮች በሦስት ይከፈላሉ፡፡ አንደኛዎቹን በፕላን አለመመራት፣ ሁለተኛው የተቀናጀ የመሬት መረጃ አያያዝ አለመኖርና ሦስተኛው ሕገወጥ ግንባታ ናቸው፡፡ 

ሪፖርተር፡- ባለፈው በየካ ክፍለ ከተማ የሚፈለግ 500 የይዞታ ማረጋገጫ ፋይል፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ መገኘቱ ተገልጾ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ይገናኝ ይሆን?

አቶ ኃየሎም፡- ይህ መረጃ ለአንተ ከደረሰ ላስተካክለው፡፡ ምንድነው የሆነው? እነዚያ  ቀበሌዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለአስተዳዳራዊ ሥራዎች ባለመመቸቱ ቀበሌዎች ወደ የካ ክፍለ ከተማ እንዲጠቃለሉ ተደረገ፡፡ ወደ የካ ክፍለ ከተማ ሲጠቃለል ግን ፋይሎቹ ተያይዘው አልመጡም ነበር፡፡ ፋይሎቹን ቦሌና የካ አልተረከቡም ነበር፡፡ ስለጠፉ አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ሆን ተብሎ አይደለም፡፡ የማይንቀሳቅሰ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ የማረጋገጥ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ ፋይሎቹን የካ ክፍለ ከተማ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የት ሄደ ተብሎ ሲፈለግ ጠፋ ተብሎ ተወራ፡፡ እኔ አስተባብሪ ሆኜ ጉዳዩን ስናጠራ ቀበሌዎች ለአስተዳደር ወደ የካ በመጠቃለላቸው፣ ግን ደግሞ ፋይሎቹ ባለመሄዳቸው ቦሌ ላይ ሲፈለጉ ሊገኝኙ ችሏል፡፡ ሰው ስላጠፋው ሳይሆን ሁኔታዎች ችግሩን እንዲፈጠር አድርገውታል፡፡ ፋይል መጥፋት ግን ይኼ ብቻ ሳይሆን እንደሀብት ካለመቁጠርና ለሌላ ዓላማ ለማዋል ሲባልም ሊጠፋ ይችላል፡፡ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ግን የፋይል መጥፋትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈታል፡፡ ያን ጊዜ ኪራይ ሰብሳቢነት አይኖርም ለማለት ሳይሆን፣ በጣም እንዲቀንስ ሊደረግ ይችላል፡፡ 

ሪፖርተር፡- ወደ ሕገወጥ ባለይዞታዎች ጥያቄ ቢመልሱን? 

አቶ ኃየሎም፡- በ2007 ዓ.ም. 44,547 ሕገወጥ ባለይዞታዎችን ለማስተናገድ አቅደን ገባን፡፡ መመርያው ዘግይቶ ነው በጥር ወር የፀደቀው፡፡ ስለዚህ ወደ ሥራ በሚገባበት ጊዜ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሰፊ የግንዛቤ መስጫ ሰፋፊ መድረኮች አዘጋጅተን ነበር፡፡ ከዚያ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ብዙ ችግሮች ገጥመውን ነበር፡፡ ሁሉን አልፈን ወደ አራት ሺሕ ካርታዎችን አትመን ለመስጠት ሞክረናል፡፡ ሥራው ጥልቅና ውስብስብ ነው፡፡ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ነው በትብብር የምንሠራው፡፡ ምዝገባውንና ማጣራቱን የምንሠራው ከማኅበረሰቡና ከኮሚቴ ጋር ነው፡፡ ከዚያ በራሳችን መዋቅር ማጣራት እናደርጋለን፡፡ ይኼን መሠረት በማድረግ ነው የምናስተናግደው፡፡ ሥራውን ግን በ2008 ዓ.ም. የማጠናቀቅ ዕቅድ ይዘናል፡፡

ሪፖርተር፡- ሕገወጥ የተባሉትን ባለይዞታዎች ወይም መሬት በወረራ የያዙትን ሕጋዊ ለማድረግ እየሠራችሁ ነው፡፡ ነገር ግን እየተቸገሩም ቢሆን መሬት ያልወረሩ አሉ፡፡ ከዚህ ሥራችሁ ተጠቃሚ ያልሆኑ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሥራችሁን ዓይተው ምን ዓይነት መርህ እየተከላችሁ ነው ቢሏችሁ ምላሽዎ ምንድነው?

አቶ ኃየሎም፡- በማንኛውም መሥፈርት ሕገወጥ ሥራ ማበረታት የለበትም፡፡ ለወደፊቱም ቢሆን፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ በሕገወጥ የተያዘ መሬት አለ፡፡ በዚህ በኩል ያልተገባ ድርጊት እየተፈጸመ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ይህ ድርጊት ሕገወጥ ስለሆነ ዕርምጃ እንወስዳለን፡፡ ነገር ግን መሬት ሳይወሩ የተቀመጡና የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸው አሉ፡፡ ወረው ደግሞ ተጠቃሚ የሆኑ አሉ፡፡ አስተዳድሩ መሬት ከመወረሩ በፊት መከላከል ነበረበት፡፡ ተወሮ ከተገነባ በኋላ የመኖሪያ ቤት ችግር  ስለነበር ነው የሚለው ሚዛን ደፍቷል፡፡ ሕጋዊ የማድረጉ ጉዳይ የመጣውም ለዚህ ነው፡፡ አሁን ሥርዓት አበጅተናል፡፡ ማኅበረሰቡ ገንብቶ እየኖረ ነው፡፡ ይኼንን ብታፈናቅል ትልቅ ችግር ትፈጥራለህ፡፡ በነገራችን ላይ መንግሥት ይህን ሲያደርግ ለመከላከል ይመቻል ወይም ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ለሁለቱም ጥቅም አለው፡፡ ለወደፊቱ ግን ይህ እንዳይከሰት ዕርምጃ ይወስዳል፡፡ ሕገወጦችን ሕጋዊ እያደረክ የምታቀብል ከሆነ ግን አደጋው የከፋ ነው፡፡ 

ሪፖርተር፡- የመሬት አስተዳድር ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ሥራዎችን መሥራታችሁ ይነገራል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ችግሮች እንዳሉም ይነገራል፡፡ እናንተ ደግሞ ግምገማ አካሂዳችኋል፡፡ የግምገማችሁ ውጤት ምን ይመስላል?

አቶ ኃየሎም፡- አመራሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት አድርጓል፡፡ የተለያዩ ሥራዎችም እየተሠሩ ነው፡፡ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል፡፡ አሁንም ቢሆን የመሬት ዘርፍ የኪራይ ሰብሳቢዎች እርጥብ ቦታ ነው፡፡ ያን መሠረት በማድረግ ትላልቅ ትግሎች አድርገናል፡፡ የተለያዩ ግምገማ ነክ ሥልጠናዎችን በየጊዜው አካሂደናል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ከማዕከል ጀምሮ አስከ ወረዳ ድረስ ባሉ መዋቅሮች ከቀላል ማስጠንቀቂያ እስከ ማባረርና ለፀረ ሙስና ኮሚሽን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ ዕርምጃ ወስደናል፡፡ በቁጥር ሲቀመጥ በ2007 ዓ.ም. 315 አመራሮችና ፈጻሚዎች ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ቁጥሩ የበዛ ይመስላል፡፡ እኛ ግን በግምገማችን ካለው ችግር አንፃር ቁጥሩ ትንሽ ነው የምንለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቅጣቱ ሳይሆን ሰው ወዳልተገባ ሥራ እንዳይገባ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ዋነኛ ሥራ በመሆኑ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተናል፡፡ ይህን አድርገን ስናበቃ ዕርምጃ ወስደናል፡፡ በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 90 በሚሆኑ አመራርና ፈጻሚዎች ላይ ዕርምጃ ወስደናል፡፡

ሪፖርተር፡- ብዙ ጊዜ የኢሕአዴግ ግምገማዎች ጠበቅ ያሉ ናቸው ይባል ነበር፡፡ በግምገማ ወቅት እዚህም እዚያም መሬት የያዙ መሆናቸው ማረጋገጫ የቀረበባቸው አመራሮች አሉ፡፡ ነገር ግን ማረጋገጫ የቀረበባቸው አመራሮች ተከታትላችሁ ቦታዎቹን ትረከባላችሁ? 

አቶ ኃየሎም፡- እኔ ወደዚህ ኃላፊነት ከመጣሁ ጀምሮ መሬት የሚተላለፈው ግልጽ ሥርዓት ይዞ ነው፡፡ በምደባና በጨረታ ነው፡፡ ሲወራ ትሰማለህ ከሆነ ሌላ ነገር ነው፡፡ በትክክል ግን መሬት በሁለት መንገድ ይተላለፋል፡፡ ድሮ ባለሥልጣናት ይዘው ነበር፡፡ ከባለሥልጣን የተጠጉ ሰዎች መሬት ይዘዋል፡፡ ባለሀብቶችም በሕገወጥ መንገድ መሬት ይዘዋል ከተባለ እንደማንኛውም ሰው ነው መልስ የምሰጠው፡፡ አሁን ባለሁበት ግን ለማንም አካል መሬት የሚሰጠው በግልጽ አሠራር ነው፡፡ ዝቅተኛውና መካከለኛው የኅብረተሰብ ክፍል በኮንዶሚኒየም ቤት ይስተናገዳል፡፡ አቅም ያለው የኅብረተሰብ ክፍል በጨረታ፣ ለማኑፋክቸሪንክ ኢንዱስትሪ ደግሞ በምደባ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አመራርም ሆነ ማንኛውም ሰው መሬት የሚያገኝበት አሠራር ዝግ ነው፡፡ የአንተ ሐሳብ ያደረ የቤት ሥራ ነው፡፡ ቀደም ሲል ግልጽ አሠራር ባለመኖሩ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሊኖር ይችላል፡፡ በተጨማሪም የምንሰማቸውም አሉ፡፡ አሁን ግን ወሮ የያዘ ካልሆነ በስተቀር የለም፡፡ ይኼ ደግሞ ትክክለኛ አሠራር አይደለም፡፡

No comments:

Post a Comment